Postpartum_depression

ስለ ድህረ ወሊድ ድብርት ማወቅ ያለብዎ 6 ወሳኝ ነጥቦች | 6 Key Points About Postpartum Depression That you Must Know

Table of Contents

1. ድህረ ወሊድ ድብርት ምንድን ነው?| Definition of Postpartum depression

ድህረ ወሊድ ድብርት | Postpartum depression አንዲት ወላድ እናት ከወለደች ከ 4 እስከ 6 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከሠት የድባቴ/ድብርት አይነት ነው ፤ ጊዜውን ገፍቶም አንዳንዴ እስከ 12ተኛው ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጀምር ይችላል። ይህ ህመም ከ10-15% የወለዱ እናቶች ላይ ይታያል ።

2. ለድህረ ወሊድ ደብርት እንዲከሰት ከፍተኛ አስተዋፅዎ የሚያደርጉ ነገሮች

✨ በእርግዝና ጊዜ ጨምረው የነበሩ ሆርሞኖች (Estrogen and Progestron) በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ
✨ ልጅ ከተወለደ በውሀላ ተያይዞ የሚመጣ እንቅልፍ ማጣት ትንንሽ ጉዳዮችን በራሳችን ማከናወን እንዲከብደን ስለሚያደርግ ይህም ተስፋ የመቁረጥ እና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እየሆኑ እንደሆነ መምሰል
✨ከእርግዝና በፊት ወይም በእርግዝና ጊዜ የነበረ ጭንቀት ወይም ድብርት
✨በበፊቱ እርግዝና ላይ ድህረ ወሊድ ድብርት ከነበረ
✨ከዚህ በፊት የነበረ የስነ ዓእምሮ ችግር ካለ
✨ከዚህ በፊት ወይም በእርግዝና ላይ የጤና መታወክ ከነበረ ወይም ደግሞ ከስራ መባረር እና ስራ ማጣት ካለ
✨የወለድሽው ልጅ የተለያዩ የጤና እክሎች ካሉት እና ህክምናና የተለየ እንክብካቤ የሚያስፈልገው ከሆነ
✨ከአንድ በላይ ህፃን ወልደሽ ከሆነ ይህም ለማጥባት እና ለመንከባከብ ከብዶሽ ከሆነ
✨በመጀመሪያ አካባቢ ጡት ማጥባት የሚያስቸግርሽ ከሆነ
✨ከትዳር አጋርሽ ጋር አለመስማማት ወይም መጋጨት ካለ
✨ቤተሰቦችሽ አብረውሽ ከጎንሽ ከሌሉ የሚደግፍሽ ሰው ካጣሽ
✨አነስተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ ነገሮችን ለልጅሽ ማሟላት ካቃተሽ
✨እርግዝናው ሳይታቀድ ፣ ሳይፈለግ እና ድጋፍ ሳይደረግለት ከተከሰተ

3. የድህረ ወሊድ ደብርት ምልክቶቹ

✨ የድብርት ስሜት ፣
✨ ከልክ ያለፈ ጭንቀት ፣
✨ ራስን የማጥፋት ሀሣብ ፣
✨ የተወለደውን ልጅ የመጉዳት ሀሣብ ፣
✨ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ፣
✨ የጥፋተኝነት ስሜት ፣
✨ ለራስ ወይም ለጨቅላው ህፃን ግድየለሽ መሆን ፣
✨ እንቅልፍ ማጣት እንዲሁም የሠውነት ክብደት በከፍተኛ ደረጃ መለወጥ ናቸው።
እነኚህ ምልክቶች ከ 2 ሳምንታት ካለፋ , ወደ ስነ-አእምሮ ሀኪም በመሄድ የህክምና እርዳታ ማግኘት የግድ ይላል።

4. ድህረ ወሊድ ድብርትን እንዴት እንከላከለው?

 • በግልፅ ትዳር አጋራችንን እና ቤተሰባችንን እርዳታ እንደምንፈልግ መጠየቅ
 • ከወሊድ በውሀላ ስላሉ ነገሮች ማንበብ ወይም ሀኪምን ማማከር
 • በጠዋት ተነሰወቶ ትንሽም ቢሆን እንቅስቃሴ ማድረግ (ባሎች ልጁን በመንከባከብ አግዙ)
 • በተቻለ አቅም ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ጊዜ አሳልፉ
 • የተመጣጠነ እና የማያጨናንቅ ምግብን ተመገቢ
 • ልጅሽ በሚተኛበት ጊዜ ለመተኛት እራስሽን አለማምጂ
 • ልክ እንዳንቺ የወለዱ እናቶች ጋር በመደወል ወይም በአካል በመገናኘት ሀሳብን ተለዋወጪ
 • እራስሽን እችላለሁ ብለሽ አሳምኚ፤ እራስሽን ዝቅ አድርገሽ አትዪ ምክንያቱም ብዙ እናቶች ላይ የሚከሰት እና በጊዜ ሂደት የሚስተካከል ስለሆነ
 • በእርግዝና ወቅት ሆነ ጡት በማጥባት ጊዜ ያለ ምንም ችግር ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኒቶች እንዲሰጥዎት ሐኪምዎን ወይም አዋላጅ ሐኪምዎን ያነጋግሩ።

5. የባሎች ድርሻ :-

ሚስትህ የምታሳየው ባህሪ የሚጠበቅ እና በሆርሞን እና በተለያዩ ነገሮች ሊከሰት የሚችል ስለሆነ ከመቼውም በተለየ አብሮነትህ እና መረዳትህ ሊጨምር ይገባል። ህፃኑን በመጠበቅ ለባለቤትህ ከጓደኞቿ ጋር ጊዜ እንድታሳልፍ እድሉን ስጣት ይህም በራስ መተማመኗን ይጨምርላታል። በጣም በደከማት ወይም ውጥርጥር ባለች ጊዜ ልጁን በመያዝ እሷ እንቅልፍ ወይም እረፍት እንድታደርግ ማድረግ። አንዳንዴ ህፃኑን ለቤተሰብ በማስጠበቅ ባለቤትህን ውጭ መጋበዝ ፣ ሲኒማ ፣ ቲያትር እና የመሳሰሉት ቦታዎች መውሰድ እና ማዝናናት።

6. ልጅ ከተወለደ በውሀላ ተያይዞ የሚመጣ እንቅልፍ ማጣት እንዴት

እንቅልፍ ለጤንነትዎ ጠቃሚ ነው። ገና የተወለደ አዲስ ልጅ ሲኖርዎት ፣ ህጻን ልጅ ለመተኛት ስለማይፈልግ ለማረፍ ወይም ለመተኛት ዘወትር በጣም አስቸጋሪ ነው:: ህጻን ልጅ ከተወለደ በኋላ እንቅልፍዎ ሊቀየር ይችላል፣ ነገር ግን አስፈላጊውን እረፍት ለማግኘት እራስዎን ለመርዳት እነዚህ ነገሮች መሞከር ይችላሉ።


በአጠቃላይ የሚፈልጉትን የ7-9 ሰዓት እንቅልፍ ለማግኘት፣ የ2-3 ሰዓት ዙሮች ጊዜ ሊተኙ ይችላሉ። በዚያን ጊዜ ፣ ለመተኛት ከመሞከር ሌላ ማንኛውንም ነገር አያድርጉ። ለመመገብ መነሳት ካስፈልግዎ ፣ ያድርጉት ፣ የሽንት ጨርቁን ይቀይሩ፣ እና ከዚያ በቀጥታ ወደ አልጋ ይሂዱ።


ጤናማ የመኝታ አካባቢ ይፍጠሩ ፣ መብራት ያጥፉ ፣ ዝቅ ያድርጉ ፣ ወይም ቀይ አምፑል ይጠቀሙ። ቲቪ ማየት አይጀምሩ ፣ ሙዚቃ አያጫውቱ ፣ ወይም ስልክዎን ሌላ የኤሌክሮኒካዊ መሳሪያዎችን አይዩ።
• ከዋና የመኝታ ሰዓት በተጨማሪ ፣ ህጻኑ ተኝቶ እያለ ይረፉ ወይም ለአጭር ጊዜ ይተኙ። ያንን ጊዜ ለቤት ሥራዎች ወይም ለሌላ ለማንኛውም ሥራ አይጠቀሙ።
• በተከታታይ ከ5-6 ሰዓት እንቅልፍ ለማግኘት ይሞክሩ – ይህም ጭንቀትዎ ወይም መሸበርዎ እንዲሻል ሊያደርግ እንደሚችል ምርምር ያሳያል።

ያስታውሱ
✨ ይህ ህመም በማንኛዋም የወለደች እናት ላይ ሊከሰት ይችላል።
✨ የስነ-አእምሮ ህክምና የሚያስፈልግሽ ምልክቶቹ ከሁለት ሳምንታት ካለፋ ነው።

ማጣቀሻ Reference

 1. https://www.acog.org/womens-health/faqs/postpartum-depression
 2. https://www.psychiatry.org/patients-families/postpartum-depression/what-is-postpartum-depression

Disclaimer:

This blog provides general information and discussions about health and related subjects. The information and other content provided in this blog, or in any linked materials, are not intended and should not be construed as medical advice, nor is the information a substitute for professional medical expertise or treatment.

If you or any other person has a medical concern, you should consult with your health care provider or seek other professional medical treatment. Never disregard professional medical advice or delay in seeking it because of something that have read on this blog or in any linked materials. If you think you may have a medical emergency, call your doctor or emergency services immediately.

The opinions and views expressed on this blog and website have no relation to those of any academic, hospital, health practice or other institution.